በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ተረፈምርቶች ፈጭቶ ወደ ፓውደር እና ግራኑዋል ፎርም ለማስቀየር የአገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ተረፈምርቶች ፈጭቶ ወደ ፓውደር እና ግራኑዋል ፎርም ለማስቀየር የአገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
በመሆኑም ተጫራቾች
- በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፤ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራች የመፍጫ ዋጋ በሚለው አምድ ስር የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ በድልዝ ገልፀው በታሸገ ኢቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት በድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፤
- ተጫራቹ የአገልግሎቱን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፤
- ትከከለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኢንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለፅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝን ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፣ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592266 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
አድራሻችን ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
በኢትዮ- ኢንጂነሪንግ ግሩኘ
የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
አዲስ አበባ
