Tender Detail

Tender Details

  • Company የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
  • Address ነቀምት ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 05-76-60-13-02
  • Website
  • Deadline20 Nov 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ የሚውል ጥራጥሬ ፣ ብዕር እህሎች፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ፤ የንጽህና መሳሪያዎች፣ ማገዶ /ግንድላ/ እና ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ የሚውል ጥራጥሬ ፣ ብዕር እህሎች፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ፤ የንጽህና መሳሪያዎች፣ ማገዶ /ግንድላ/ እና ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 የመንግስት ስራዎች ቀን ለእያንዳንዱ ሰነዶች የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በመክፈል ከነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ጥሩ የአቅራቢነት ባህርይ ያላቸው መሆን አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እህሎች ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ የአንድ ፖስታ ጋር በሰም በታሸገ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር የተጠቀውን / "Specification" ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋውን በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶከመንታቸውን ኦሪጅናል ቴክኒክና ፋይናንስ በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ትልቁ ፖስታ እስከ 11/03/2017 ዓ.ም ድረስ በቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው ሣጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ1፡30 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 12/03/2017 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት እያግደውም።
  8. የጨረታው ሳጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  9. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቶች ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር በሚያደርገው የውል ስምምነት መሰረት ነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በሚገኘው ከውል ሰጪው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል፡፡
  10. መ/ቤታችን በሚያወዳድረው እህሎች ሆነ ሌሎች የተጠየቀውን "Specification" ብዛት ላይ እንደየአስፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል፡፡
  11. ተጫራቾች ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቶች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀ ከአምስት ቀን በኋላ በውል ሰጪው መ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታውን ከአሸነፉ በኋላ የገበያ ዋጋ ጨምሯል ብለው ማመልከቻ የሚያቀርቡ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡

ማሳሰቢያ

ዋጋ ከመስጠትዎ በፊት መመሪያውን በትክክል ያንብቡ

 ስልክ ቁጥር፡- 05-76-60-13-02/09-17-08-75-17

 

የነቀምቴ መምህራን ትምህር ኮሌጅ

 

Save Tender