በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የጉደያ ቢላ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ለመንገድ ጥገና የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎችን እስከ ሥራ ቦታ ማለትም አስከ ቢላ ከተማ ድረስ ማቅረብ የሚችል ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የጉደያ ቢላ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን የጉደያ ቢላ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ለመንገድ ጥገና የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎችን እስከ ሥራ ቦታ ማለትም አስከ ቢላ ከተማ ድረስ ማቅረብ የሚችል ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የማሽኑ ዓይነት
- ግሬደር 160 HP cater pillar የተመረተበት ጊዜ እ.ኤ.አ.አ 2012 ወደዚህ የተመረተና 180 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፡፡
- እስከቫተር (excavator) የተመረተበት ጊዜ እ.ኤ.አ.አ 2012 ወደዚህ የተመረተና 255 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ዳምፕ ትራክ እና ሻወር ትራክ ሰገረጋንቲ ጭነት እንዲሁም ለውሃ ማመላለሻ የሚያገለግል።
- ቀላል ተሽከርካሪ (ፒክ አፕ) ለሰራተኞች ማመላለሻ የሚሆን ማቅረብ የሚችል።
- ሮለር (8-10) ለመንገድ ሥራ የሚያገለግል ማቅረብ የሚችል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ለማሽኖች ሁሉ ነዳጅ እና ቅባት እንዲሁም አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች የሚያቀርበው ያሸነፈው ተጫራች ይሆናል።
የመወዳደሪያ መስፈርት
- ማንኛውም ተጫራች የ 2016 ዓ.ም ግብር የከፈለ እና ንግድ ፍቃዱ የታደሰ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የቫት (VAT) እና ቲን (TIN) ተመዝጋቢ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር የሚያገለግል ዶክዩሜንት (Specification of materials) የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ከፍሎ የጨረታ ዶክመንት በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ማለትም ከ20/2/2017 እስከ 10/3/2017 ዓ.ም ከጉደያ ቢላ ወረዳ ገቢ ጽ/ቤት መውሰድ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ብቻ ለሁሉም ማሽኖች ማስያዝ አለበት ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በገዙበት ሠነድ ላይ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ኦሪጅናል ቴክኒክ እና ፋይናንስ እንዲሁም ኮፒ ፋይናንስ እና ቴክኒክ በተለያየ ፖስታ አሽገው ከ CPO ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽገው በጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛው ቀን ማለትም በ11/3/2017 ዓ.ም ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11/3/2017 ዓ.ም እስከ 3፡30 ሰዓት ቆይቶ በዚያውም ቀን በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታውን ከመከፈት አያግድም ።
- ማንኛውም ተጫራች ማሸነፉ በተረጋገጠ በኋላ ለውጭ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንከ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት
- ጨረታውን ያሸነፈ የቅድመ ከፍያ (Advance Payment) ለመውሰድ ከታወቀ ባንከ (Unconditional bond) ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ስነድ ላይ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ አለባችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማሽኑን ሊብሬ ማቅረብ አለበት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሠረት ማሽኖችን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል ቅድመ ክፍያ የሚከናወነው ማሽኑን ወረዳው እንደ ደረሰ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች with holding tax 2% ለመከፈል ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማሽኑን መግለጫ (Spesfication) ማቅረብ አለበት ፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ አካል ከ3-5 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0936008854/0917094668 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የጉደያ ቢላ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
