በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፓርት መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሌ ዘመራ ጋላፊ ከባድ መንገድ ጥገና ፕሮጀከት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ያገለገሉ የተለያየ መጠን ያላቸው እቃዎችን፣ የተለያዩ ያገለገሉ እምፔር ያላቸው ባትሪዎች እና ባዶ አስፋልት በርሜሎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን
ያገለገሉ ዕቃዎች ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፓርት መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሌ ዘመራ ጋላፊ ከባድ መንገድ ጥገና ፕሮጀከት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ያገለገሉ የተለያየ መጠን ያላቸው እቃዎችን፣ የተለያዩ ያገለገሉ እምፔር ያላቸው ባትሪዎች እና ባዶ አስፋልት በርሜሎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት አገልግሎት የተዛመደ የ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በፕሮጀክታችን የሂሳብ ቁጥር 1000322978654/ECWC MIL, Gal & DICHO JUN DOBI PROJ ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበት የባንከ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ሚሌ ሠመራ መንገድ ጥገና ፕሮጀከት ግዥ፤ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርበው ተጫራች ሲሆን የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሚሌ-ሰመራ-ጋላፊ ከባድ መንገድ ጥገና ፕሮጀክት ግዥ፤ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የታሸገ የጨረታ ሰነድን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ከ10 በመቶ /10%/ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO ወይም በባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው ሳጥን መዝጊያ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ የወጣበት ቀን ተቆጥሮ በ15ኛው ቀን ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን መከፈቻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ የወጣበት ቀን ተቆጥሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ሚሌ ሠመራ ጋላፊ ከባድ መንገድ ጥገና ፕሮጀከት ግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሠነዱን ከገዙበት ቦታ ይሆናል፡፡
- ፕሮጀክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0954760540 ወይም 0930497786
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን
የሚሌ‐ሰመራ‐ጋላፊ‐ከባድ መንገድ ጥገና ፕሮጀክት
