በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ለማከናወን ካቀዳቸው ግዥዎች ውስጥ የእንስሳት መድሃኒት እና የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ሠመራ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ለማከናወን ካቀዳቸው ግዥዎች ውስጥ የእንስሳት መድሃኒት እና የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ጣደሬታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያለው
- ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት እና
- የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይርክተሬት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ (C.P.O) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታው ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፈ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና ለተጠየቀው የእንስሳት መድሃኒት ናሙና ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረመ በኋላ ወዲያውኑ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡት የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በዕለቱ 4፡30 ሰአት በአፋር ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በቢሮ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ክፍል በቢሮ በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ
ሠመራ
