Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
  • Address አራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ ዋስትና ህንፃ ከቸርቸር ጎዳና ወደ እሪ በከንቱ በሚወስደው መንገድ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011118132208
  • Website
  • Deadline08 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Stationery Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች እና የዩፒኤስ ባትሪ በ2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ


ለመጀመሪያ  ጊዜ  የወጣ  ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

   የጨረታ  ቁጥር  አ/አ/ኢ/ቴ/ል/ቢ/ግ/ጨ/ቁ-003/2017

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች እና የዩፒኤስ ባትሪ በ2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥዎች፡-

ሎት 1-የዩፒኤስ ባትሪ

ሎት 2- ካኖን ፎቶ ኮፒ ቀለም ጥቁር

ሎት 3- ካኖን ፎቶ ኮፒ ቀለም ከለር

ሎት 4- ካኖን ፎቶ ኮፒ ቀለም ከለር

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች/ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚገልጽ የምስከር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነታቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ግብር መክፈላቸውን የሚያሳይ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት1 እስከ ሎት 3 የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ 13ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ከፍል በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ሰነድ ውስጥ የተገለፀውን ማለትም ከሎት-1 እስከ ሎት-3 ብር 40,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በማቅረብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለማቅረብ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ፈቃድ የተሰጠው መሆኑን የሚገልፅ ሰነድ እንዲቀርብ ይጠበቃል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሲፒአ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉብትን ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ቀን በመቁጠር ከሎት 1 እስከ ሎት 3 በአዲስ ዘመን ለወጡ ጨረታዎች ጨረታው በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሯችን 14ኛ ፎቅ በሚገኝው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  7. እያንዳንዱ ተጫራች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0118132208

አድራሻ፡- አራዳ ከ/ከተማ ፒያሳ በሚገኘው የመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ ዋስትና ሕንፃ ከቸርቸር ጎዳና ወደ እሪ በከንቱ በሚወስደው መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ልማት ቢሮ 13ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ከፍል፡፡

 

በአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደር ኢኖቬሽንና  ቴክኖሎጂ  ልማት  ቢሮ

Save Tender