በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወሎ ዞን የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወሎ ዞን የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
ሎት:- 1 - የፅህፈት መሳሪያዎች፣
ሎት:- 2 - የፅዳት እና ሌሎች አላቂ እቃዎች፣
ሎት፡- 3 - የደንብ ልብስ እና ተያያዥነት ያላቸው አልባሳት፣
ሎት፡- 4 - ህትመት፣
ሎት- 5 - ኤሌክትሮኒክስ፣
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው;
- የግዥ መጠን ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቀረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሁሉንም እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሆስፒታሉ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሆነ የውል ማስከበሪያ 10% የሚያስይዝ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ባሸነፈው መሰረት ውል ባይወስድ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ስለዚህ ለጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሁለንም የስራ ዘርፎች የጨረታውን ሰነድ በመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመቅረብ የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ ከፍሎ መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በኤንቨሎፕ ላይ ስማቸውንና ስልከ ቁጥር በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 71 በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሎት ስለሆነ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ድምር መሰረት ነው አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃዎች በሆስፒታሉ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሆስፒታል ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09-63-60-64-73 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
