የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ የእቃ እና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሎት 1 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ግዥ ሎት 2 ለህጻናት ማቆያ ክፍል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግዥ ሎት 3 የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ ማግኘት ይፈልጋል::
Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ የእቃ እና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሎት 1 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ግዥ ሎት 2 ለህጻናት ማቆያ ክፍል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግዥ ሎት 3 የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ ማግኘት ይፈልጋል:: ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተመሰከረ /CPO/ ለሎት 1. 20,000.00 ብር ለሎት 2. 10,000.00 ብር ለሎት 3. 100,000.00 ብር ለተጠቀሰው ዕቃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከቢሮአችን ከመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት እና ቢሮ ቁጥር 101 ሰነዱን በሶፍት ኮፒ ፣በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ለሎት 1 እና 2 ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ለሎት 3 ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ፖስታ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው 7 ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል:: ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ በ7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት:: ይህን ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል::
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡- 011 122 64 56
አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
