በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግዥ ጨረታ አውጥቷል ስለሆነም ብቁ የሆኑ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
ግልጽ የግዥ ጨረታ የጨረታ ቁጥር
የጨረታ ቁጥር 02/2017
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግዥ ጨረታ የሚያስፈልገውን በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 01 ፡- የመኪና ጥገና
ሎት 02 ፡- የካዝና ግዥ
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No. ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሠነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታውን ሰነድ በነፃ ይወስዳሉ ከአደራጃቸው ተቋም ወቅታዊ የሆነ በአድራሻችን የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ብር
ሎት 01፡- የመኪና ጥገና -------------------- 20,000.00 / ሀያ ሺህ ብር/
ሎት 02፡- የካዝና ግዥ ------------------- 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንከ የተረጋገጠ / ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሰነዱ የሚመልሱበት በ11ኛው ቀን የስራ ሰዓት ተመልሶ የስራ ቀን በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ከ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በቢሮ ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶና ኦርጅናሉ ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ በእናት ፖስታ ታሽጓ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብና ሌሎችንም ዕቃዎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሠረት ዋጋቸውን በአግባቡ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
በጨረታ ሠነድ ክፍል 4, 6 እና 9 የተቀመጡ ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሞልተው ያልቀረቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስረከቢያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸው ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚቀርብበት ዕቃ/ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት ዕቃ ከገበያ ላይ ገዝተው ለሚወዳደሩት እያንዳንዱ ምርት/ዕቃ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፤
- ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአራት ሊሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ አዲሱ የክፍስ ከተማ ህንጻ ላይ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 የአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን
ስልክ ቁጥር፡- 0111 26 57 45
የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
የመንግስት ግዥ ቡድን
