Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ደብረ ማርቆስ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0587713052
  • Websitehttps://www.era.gov.et
  • Deadline29 Oct 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Hand Tools And Workshop Equipment

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ እቃዎች የእጅ መሳሪያዎች (Hand Tools) እና ሌሎች ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


የሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ቲ-02/2017

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ እቃዎች የእጅ መሳሪያዎች (Hand Tools) እና ሌሎች ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የታደሠ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች አስፈላጊውን ማስረጃ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የእቃዎችን ሁኔታ በዲስትሪክቱ ግቢ በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 20% ያላነሰ በባንከ በተረጋገጠ ዋስትና (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 15 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጐ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ቅጥር ግቢ በሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ወይም ሲፒኦ (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ እንደተገለፀ አስፈላጊውን ውል በአካል ቀርቦ መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈፅም ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር 1000322269165 (ERA D/M Dist. "B" ገቢ በማደረግ የባንከ ደረሰኝ በመያዝ ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ቢሮ ቁጥር 15 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይቻላል፡፡ ማንኛውም ተጫራች የሰጠው መወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡ አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ገንዘብ ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587713052, 0911984416 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ

መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

Save Tender