በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ወጪ የሚውል ከአለም ባንክ በተገኘ በጀት ድጋፍ ኖራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 108/17
የሀገሪቱ የክልሉ ስም፡- ኢትዮጵያ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት/
የፕሮጀክቱ ስም፡- የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀከት
የፕሮጀክቱ ቁጥር- P178566
የብድር ቁጥር 7156-ET
የግዥው አይነት የኖራ ግዥ
የግዥ መለያ ቁጥር :- EI-SER-ESRP-437162-GO-RFB
- በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ወጪ የሚውል ከአለም ባንክ በተገኘ በጀት ድጋፍ ኖራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ 16,209 ኩንታል ኖራ ለመግዛት ብቁ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከ16/02/2017 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እስከ ከሰአት 11፡30 ድረስ ከቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እየመጣችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ክፍያው የሚፈጸመው በጥሬ ገንዘብ ይሆናል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 75.000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች እስከ 16/03/2017 ዓ/ም ጠዋት 4፡00 ሰአት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው ስለሚከፈት የአከፋፈቱን ስነስርአት መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 16/03/2017 ዓ/ም ጠዋት በ4፡10 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡ ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የቢሮ አድራሻ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ወደ ዲላ ዩኒቨርስቲ መሄጃ መንገድ የዲላ መምህራን ትምርት ስልጠና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ
ስልከ ቁጥር 046-131-01-34
ዲላ ኢትዮጵያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
