ድርጅታችን በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ፣ የሰርቪስ እና የቀላል ተሸከርካሪዎች ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት
የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ፤ የሰርቪስ እና የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማዎች
ጨረታ መመሪያ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/ቅ/007/17
ድርጅታችን በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ፣ የሰርቪስ እና የቀላል ተሸከርካሪዎች ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራቱ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝር መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአቅ/ፋ/ማ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)፤ በታሸገ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴከኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የቴክኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናንሻል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሻል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 03 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ/የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አገልግሎት የሚውል ያሸነፈበትን ጥቅል ዋጋ ብር 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል ይፈፅማል፤
- ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀር ብዛት በ25% ለመጨመር/ለመቀነስ መብት አለው::
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ከድርጅታችን የጎማ ግዥውን ለአንድ ዓመት እና እንደ አስፈላጊነቱ ከአንድ ዓመት በላይም ሆኖ ከሁለት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የማዕቀፍ ግዥ ውል ስምምነት በመፈራረም አቅርቦቱን ሊያቀርብ የግዴታ ውል የሚገባ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 011 439 00 75/ 011 439 10 27
መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ:- አቃቂ ቃሲቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ስፌት ትሬን ባትሪ መሸጫ
ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው፤
የእለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት
