የአዲስ አበባ ትራንስፓርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የተለየዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ሎት 1:- የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችና የተለያዩ የመኪና ጎማና ባትሪዎች፤ ሎት 2፡- የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 3 :- የጽዳት ዕቃዎች! ሎት 4 - የደንብ ልብስ :- በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ትራንስፓርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የተለየዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ሎት 1:- የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችና የተለያዩ የመኪና ጎማና ባትሪዎች፤ ሎት 2፡- የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 3 :- የጽዳት ዕቃዎች! ሎት 4 - የደንብ ልብስ :- በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፤
- ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒከ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት አንድ ብር 20,000.00፣ ሎት ሁለት ብር 4,000፣ ሎት ሶስት ብር 3,000.00፣ ሎት አራት ብር 20,000.00 CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማ፤ በእያንዳንዱ ኦርጅናል ዶክመንት ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ እና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
- ማሳሰቢያ ፦ መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ :- መገናኛ ስሪ ኤም ሞል 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 - 639 - 30 -10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የትራንስፖርት ቢሮ
