Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋአለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-225-15-62
  • Website
  • Deadline10 Nov 2024, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery

በሲ/ብ/ከ/መንግሥት ሥራና ከህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት አላቂ የጽ/መሣሪያዎች የአይ.ሲ.ቲ. የኮንስትራክሽን የአይ.ኢ.ኤም.ድ፣ የቢ.ኢ.አይ፣ የጋርመንት፣ የሆቴል፣ የአግሮ ፕሮሴሲንግ እና የተለያዩ ማሸነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋአለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሲ/ብ/ከ/መንግሥት ሥራና ከህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት አላቂ የጽ/መሣሪያዎች የአይ.ሲ.ቲ. የኮንስትራክሽን የአይ.ኢ.ኤም.ድ፣ የቢ.ኢ.አይ፣ የጋርመንት፣ የሆቴል፣ የአግሮ ፕሮሴሲንግ እና የተለያዩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ በግብር ከፋይነት የተመዘገበ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉበት የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት በይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፁት የሎት ዓይነቶች በአንዱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙ በኋላ የዋጋ ዝርዝር ሲሞሉ ከሰነዱ ውስጥ የማይፈልጉትን ገፆችን ቀዶ ማውጣት የተከለከለ ነው፡፡
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልፅ በመሙላት በማኅተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚሞላው ዋጋ (15%) ቫት ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼከ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማዘጋጀት ኦርጂናል እና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 30% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
  7. ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል የማይዋዋል ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፣
  8. ተጫራቾች ያሸነፉትን የእያንዳንዱን ዕቃ ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ መጓጓዣ እስከ ኮሌጁ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛውም ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያውኑ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በመከፈቻው ሰዓት የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም። የጨረታው መከፈቻ ቀን ወይም 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-225-15-62 መጠየቅ ይችላሉ።

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት

ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

የይርጋአለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender