በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጆና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ፤ የጽዳት እቃዎች ግዥ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጆና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ፤ የጽዳት እቃዎች ግዥ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ ቤታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ማሰራት የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር ለጽህፈት መሳሪያዎችና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለሌሎች እቃዎች ብር 100/አንድ መቶ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለደንብ ልብስ ግዥ የተዘጋጁና ብትን ጨርቅ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ፣ ለጽህፈት መሳሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ/ ፤ ለጫማ 5000 /አምስት ሺህ ብር/፤ የኤሌክትሪክ ግዥ 10000 /አስር ሺህ/፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና 5000 /አምስት ሺህ ብር/ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ 10000 /አስር ሺህ/፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል። ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸው ለእቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10/አስር/ ቀናት ለግ/ንብ/አስ/ቡድን በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
አድራሻ፡- አማራ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ፣
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን
የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
