የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሽዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የጽሕፈት መሣሪያ /አላቂ እቃዎች/ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ሽዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሽዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የጽሕፈት መሣሪያ /አላቂ እቃዎች/ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘመኑ የታደሱ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር መለያ ቁጥር /Tin No/ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት የሚችል ሲሆን ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞ/ወ/ወ/የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በወጣበት በ15ኛው ቀን 1፡30 ይዘጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በሞ/ወ/ወ/ በሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልከ ቁጥር 0116250497 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
ይህ ማስታወቂያ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድና በአላት ቀን የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀናት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
በአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የሰሜን ሸዋ
ዞን አስተዳደር የሰላ ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
