የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፓሬሽን ለኮርፓሬሽኑ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ፋስት ሙቪንግ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢንሥኮ-ማእከል ግዥ/ብግጨ 02/2017
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፓሬሽን ለኮርፓሬሽኑ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ፋስት ሙቪንግ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።
1. የተለያዩ ፋስት ሙቪንግ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ ግዥ፤
ተጫራቾች በዘርፉ ለ2016/2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ/ ጨረታ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፡ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፡ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት/TIN/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፐሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው::
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 450.00 (አራት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ከጥቅምት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡00- 10:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ማዕከል ግዥ ዋና ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ጥቅምት 29/2017 ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቶች ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ፡- የተለያዩ ፋስት ሙቪንግ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ ግዥ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድ እና ቼከ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን በግልጽ ክፋፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግና ኮፒ እና አሪጅናል የፋይናንሻል እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አድራሻ ከታች ተገልጿል።
7. ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች አንድ የቴክኒካል ሰነድ ኮፒ እና አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ነው፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል።
9. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር፡- 011 416 7345/0114 669 336 በመደወል መጠየቅ ይቻላል
አድራሻ: ቢሾፍቱ በሚወስደው መንገድ በቅሎ ቤት ከዳሸን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ፊት ለፊት።
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አገልግሎት
