በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ጥሬ ስንዴ የማስፈጨት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ውል ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ
የጨረታ ማስታወቂያ
የገዥ መለያ ቁጥር የኮ/አ/ወ/ዕዝ ግ.ጨ 02/2017
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት ማለትም፡-
1. ሎት 01 ጥሬ ስንዴ የማሰፈጨት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ውል ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች፣
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አገልግሎት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ተዛማጅነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ስም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት አዲስ አበባ አምባሳደር ቴያትር ፊት ለፊት በሚገኘው መስሪያ ቤታችን ግዥ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 011 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 14/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 29/02/2017 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 29/2/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤታችን ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 011 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 0115310019 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ
