Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን ከታች በዝርዝር በተገለፀው መሰረት የወተት ላሞች እርባታ የህንፃ እና የሞጆ የብሎኬት አጥር ግንባታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን ከታች በዝርዝር በተገለፀው መሰረት የወተት ላሞች እርባታ የህንፃ እና የሞጆ የብሎኬት አጥር ግንባታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

የጨረታ አይነት

እና ቦታ

ደረጃ

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (የማይመለስ በብር)

የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የመዝጊያ ቀን

የመዝጊያ ሰዓት

የመክፈቻ ሰዓት

1

የሎት አንድ

የወተት ላሞች እርባታ የህንፃ ግንባታ /አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና መ/ቤት

GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ

 

700

ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም

 

4፡00

 

4፡30

2

የሎት ሁለት

የሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የብሎኬት አጥር ግንባታ

(ሞጆ ከተማ)

GC-7/BC-7 እና ከዚያ በላይ

200

ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

 

 

4፡00

 

4፡30

 

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

  1. ደረጃቸው ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው ሆኖ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ እና ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አ.ማ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከላይ በየሎቱ በተገለፀው ብር መሰረት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ አንድ ተጫራች መጫረት የሚችለው በአንድ ሎት ብቻ ነው ::
  2. ተጫራቾች ለጨረታው በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ብቻ በግልፅ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና (ለ120 ቀናት የሚቆይ) ማስከበሪያ ለሎት-1 ብር 500,000.00(አምስት መቶ ሺህ) እንዲሁም ለሎት-2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ120 ቀናት የጸና ይሆናል።
  4. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  5. እያንዳንዱ ጨረታ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡
  6. ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውለታ ገብተው ግንባታ እያከናወነ የአፈፃፀም ደረጃቸው ከ70% በታች የሆነ ተቋራጮች በጨረታው ላይ መወዳደር አይችሉም ::
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ 0114-70 90 95/011442-07-97/0114-42 36 08

አዲስ አበባ

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን

Save Tender