Tender Detail

Tender Details

  • Company በድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-15-75-76-92
  • Website
  • Deadline06 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌትሪክና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የትምህርት መርጃ እና የቧንቧ እቃዎችን መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መስፈርት መሰረት ድሬዳዋ ሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌትሪክና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የትምህርት መርጃ እና የቧንቧ እቃዎችን መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መስፈርት መሰረት ድሬዳዋ ሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና በ2016 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ባቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ 3000.00 (ሶስት ሺህ ብር) ቢድ ቦንድ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  5. በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ይህ ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ተዋውለው ያሸነፉበትን ዕቃዎች በሙሉ በ10 ቀናት ውስጥ ድሬዳዋ ሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በማምጣት ለንብረት ከፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የግዢ መደብ ላይ የጨረታ መደበኛ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ድሬዳዋ በሚገኘው የሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት ብር 300 ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት በሚወዳደርባቸው የግዢ መደቦች ላይ በዝርዝር ለቀረቡት እቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

ሆኖም ጨረታ ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት የሌለው ስለሆነ ከጨረታው ውጪ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

ስልክ ቁጥር:- 09-15-75-76-92/09-37-68-74-73/09-15-00-75-24/

 

በድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Save Tender