Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለክልሉ ተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የቀረቡትን በሎት አንድ፡- ፖሊ ባግ እና በሎት ሁለት፡- የአቮካዶ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር 82/17

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለክልሉ ተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የቀረቡትን በሎት አንድ፡- ፖሊ ባግ እና በሎት ሁለት፡- የአቮካዶ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የዕቃው አገልግሎቱ ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ

የሚታሸግበት ሰዓት

የሚከፈትበት ሰዓት

መክፈቻ ቀን

1

ፓሊ ባግ ባለ 20 ሴ/ሜ

በኪ/ግ

5000

 

 

1

 

 

50,000

 

 

9:00

 

 

9:05

 

ፓሊ ባግ ባለ 18 ሴ/ሜ

በኪ/ግ

15,000

ፓሊ ባግ ባለ 10 ሴ/ሜ

በኪ/ግ

10,000

2

የአቮካዶ ዘር

በኪ/ግ

30,000

2

20, 000

10:00

10:05

 

 

በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
  • በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25/2/2017 ዓ.ም ሎት አንድ 9፡00 ሰዓት፡ ሎት ሁለት 10፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል በዲላ ከተማ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው ግብርና ቢሮ የመ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሎት አንድ እና ሎት ሁለት 10፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶችን በአንድ ፖስታ በማዘጋጀት በቢሮው ግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ስምምነት ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  • የጨረታው ሳጥን በ25/2/2017 ዓ.ም ሎት አንድ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ይከፈታል፣ ሎት ሁለት በ10፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 10:05 ሰዓት ይከፈታል፤ ተጫራቾች /ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል፡፡
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ፡- 0461310134 ይጠቀሙ።

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ

Save Tender