Tender Detail

Tender Details

  • Company የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address አዲስ አበባ, ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ዩንሳ የሚወስደው መንገድ አሌክስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የፍርድ ቤቱ ፎቅ 5 ቁጥር የፋይናንስ ክፍል ያገኙናል፡፡, Phone: 09-24-11-38-72
  • Website
  • Deadline02 Nov 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ከ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ከ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከ100,000 ብር ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በገንዘብና ትብብር ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በማይመለስ 100 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/በታች ማቅረብ አይቻልም፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  7. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
  8. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል።
  12. የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ፡ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ዩንሳ የሚወስደው መንገድ አሌክስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የፍርድ ቤቱ ፎቅ 5 ቁጥር የፋይናንስ ክፍል ያገኙናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 09-24-11-38-72

 

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender