አዋሽ ባንክ አ.ማ የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 ከመውጣቱ በፊት የውጭ ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን የሚከተሉትን አክሲዮኖች የኢትዯጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
አዋሽ ባንክ
Awash Bank
የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ አ.ማ የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 ከመውጣቱ በፊት የውጭ ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን የሚከተሉትን አክሲዮኖች የኢትዯጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የጨረታ ምድብ (ሎት) |
ለጨረታ የቀረቡ አክሲዮኖች ሰርተፍኬት ቁጥር |
የአክሲዮኖቹ ብዛት |
የአንዱ አክሲዮን መነሻ ዋጋ |
የአክሲዮኖቹ ጠቅላላ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
07183፣ 08968፣ 09974፣ 12402፣ 17881 ፣ 18748፣ 41848፣ 24820፣ 26352፣ 31699፣ 31924 እና 54037 |
234 |
1,000.00 |
234,000.00 |
|
2 |
845፣ 359፣ 05701፣ 06513፣ 01351፣ 01895፣ 03490፣ 04623፣ 08499 እና 53977 |
59 |
1,000.00 |
59,000.00 |
- የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/73/20 ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የውጭ ዜጎች እና ድርጅቶች በጨረታው በመሳተፍ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ክጨረታው ቀን በፊት ከባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ብር 200 (ሁለት መቶ) ከፍለው በመውሰድ ቅጹን ሞልተው በኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስስ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ድረስ ከባንኩ ዋና መቤት ጀርባ ባንኩ በተከራየው ኢያሜክስ ህንፃ የመሬት ወለል ላይ ባለው የባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት ቦታ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አከሲዮኖቹን ተጫርተው የሚገዙበት ዋጋ ¼ ‰ (እሩቡን) በአዋሽ ባንክ ስም በተሠራ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ክዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች የቀረበ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- በአንድ ሎት (ምድብ) የቀረቡ አክሲዮኖችን ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያሳይ የታደስ መታወቂያ፤ የመንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ደግሞ ቢጫ (የሎው) ካርድ እና ፓስፓርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች የጨረታ ማስክበሪያ ማስያዝ ያለባቸው በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሲሆን ጨረታውን ካሸነፉም ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ብቻ ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት /5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- ተለያይተው የቀረቡትን ሎቶች (ምድቦች) መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ምድብ (ሎት) በተለያየ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦውም ተለያይቶ መቅረብ አለበት:
- በሌሎች ሕጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው።
- ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
“ይህ ማስታወቂያ እንዲተላለፍ በኢትዯጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ማረጋገጫ አግኝቷል”
አዋሽ ባንክ
ለተጨማሪ መረጃ 0115-57-00-92/0115571823
ፓ.ሳ.ቁ 12638
አዲስ አበባ
