Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011637 58 03
  • Website
  • Deadline29 Oct 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Industry And Factory

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባቄሎ ቀበሌ አካባቢ ጣን አምባ ደን ቦታ ላይ በምርት ዘመኑ የሚመረት የግንድ ተረፈ ምርት እና በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)


ግልፅ  የሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባቄሎ ቀበሌ አካባቢ ጣን አምባ ደን ቦታ ላይ በምርት ዘመኑ የሚመረት የግንድ ተረፈ ምርት እና በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መረጃ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:: የተረፈ ምርቶቹን አይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታው መመሪያ ሰነድ ማግኘት ይቻላል ወይም በፋብሪካው እና በደን ቦታ ላይ በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፣ የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 200 ብር ከፍሎ መግዛት ይችላሉ::

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታው መመሪያ ላይ በተገለፀው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሲፒኦ(CPO) ማስያዝ አለባቸው::
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 02፡00 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይሆናል ሆኖም ግን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል::
  4. የጨረታ መከፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ወይም በማግስቱ  4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ይከፈታል::
  5. ተጫራቾቹ ከሥራ መስኩ ጋር ተያያዥነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የVAT እና TIN ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤ በውከልና የሚወዳደሩ አካላት ከፍትህ ወይም ከሰነዶች ማረጋገጫ ህጋዊ የውከልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው::
  6. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

➢ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116375308 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::

 

ደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Save Tender