Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address በጋርዱላ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-7-74-03-44
  • Website
  • Deadline28 Oct 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃ እና የመኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ፡-

    1. የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃ እና
    2. የመኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው፤
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦሪጅናሉ ላይ ኦሪጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፤ 15ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል፡፡
  8. ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በግዥና ንብረት አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
  10. የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊዎች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ ጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መጋዘን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቢያንስ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት መቆየት አለበት፡፡
  13. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-7-74-03-44 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender