Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር
  • Address በምስራቅ ጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 2510463210158
  • Website
  • Deadline01 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት G+4 የአስተዳደር ህንጻ የውቅር /Structural Parts of the Building/ ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር


የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት G+4 የአስተዳደር ህንጻ የውቅር /Structural Parts of the Building/ ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሰረት ፦

  1. እስከ GC ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በBC ለሚወዳደር ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያለው መሆን ይኖርበታል፤
  2. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ ቲን ነምበር ያላቸው ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣ በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኦን ላይን የተመዘገበና ከሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ከሚያቀርቡት ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፣
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን በአንድ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማለትም  1 አርጅናል እና 2 ኮፒ በመለየያት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዢ/ን/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁ.1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፤
  7. ጨረታው በ 21ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ላይ በም/መስቃን ወረዳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አዳራሽ ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይታገድም፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ /የህዝብ በዓል/ ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዳቸው ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ም/መስቃን ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ግ/ን/አ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  10.   መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11.   አዲስ በወጣው መመሪያ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት የሂሳብ ስህተት  ማስተካከያ/Arthimetic Eror/ ከ 2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ::

ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር (+251) 046 - 321 – 0158 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

♦ የህንጻው ግንባታ የሚከናወንበት ቦታ ተጫራቾች ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ቦታውን መጎብኘትና  መጎብኘታቸውን የሚያስረዳ መረጃ ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender