የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከሎት 1 (አንድ) እስከ ሎት 3 (ሦስት) የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር CCJB01/2017
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከሎት 1 (አንድ) እስከ ሎት 3 (ሦስት) የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መወዳደሪያ መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃሰን፡፡
ሀ. የግዥ ዓይነቶች
ሎት 1፡-የቢሮ ፈርኒቸሮች
ሎት 2፡-የጣት አሻራ ማሽን
ሎት 3፡-የመታወቂያ ማተሚያ ማሽን
ለ. መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- የዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም በቼክ ለሁሉም የሎት ዓይነቶች ለእያንዳንዳቸው ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺ ብር/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለጨረታ ሠነዱ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመከፈል ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) 4ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴከኒካል እና ፋይናሻል ለየብቻ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ በጉምሩክ ኮሚሽን ዋናው መ/ቤት ማስገባት ይችላል፣
- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፣
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- የቅ/ጽ/ቤት በፍላጎቱ ላይ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
አድራሻችን ፡ - ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05
ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 0904252386 0910208950 ወይም
0921822252
E-mail addres:- jijccarchive@gmail.com
የጅጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
