ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት እና ለፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈፀም ከተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 008/2017
ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት እና ለፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈፀም ከተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክ ወረቀት፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደስ ታክስ ክሊራንስ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
6. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የሀዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው ከመስከረም 29/2017 እስከ ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም እየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጭን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ ዴስክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ
