Tender Detail

Tender Details

  • Deadline21 Oct 2024, 10:39 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት አመት ለክ/ ከተማው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች (Dozer, Roller, Dam Track, Grader, shower Track and Back Loader) አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት አመት ለክ/ ከተማው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች (Dozer, Roller, Dam Track, Grader, shower Track and Back Loader) አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት / መረጃዎች በማቅረብ/ በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. በአቅራቢ ስም ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
  4. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሚገልጽ ማስረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ተከታታይ የስራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር/ በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡
  8. ጨረታው በ 16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልከ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ዝጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል ። 
  10. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊው ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊ ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ /ለመንግሥት ገቢ/ ይሆናል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከተፈ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  13. የመንግሥት የፋይናንስ ህግ እና መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. ተጫራቾች የሚፈለጉ ስለ ማሽነሪዎች፤ መኪኖች እና ሻወር ትራክ የሚገልጽ መረጃዎችን /ሊብሬ/ በሙሉ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  16. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 445 01 82 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት

Save Tender