በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደሴ ዲስትሪክት የሚገኝ አንድ አይሱዙ NPR71H ተሽከርካሪ ጋቢና ሙሉ በሙሉ የመቀየር እና የጥገና ሥራ ማሰራት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡_ EEU//D/D0001/2017
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደሴ ዲስትሪክት የሚገኝ አንድ አይሱዙ NPR71H ተሽከርካሪ ጋቢና ሙሉ በሙሉ የመቀየር እና የጥገና ሥራ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ያልታገደ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ምድር ቤት ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- አድራሻ፡- ደሴ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ምድር ቤትየደሴ ዲስትሪክት ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮ ግዥ ክፍል የስልክ ቁጥር -033-312-0983
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና “DESSE DSIRICI ELECTRIC UILITY" በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደሴ ዲስትሪክት ኤሌክትሪክ አገልግሎት
