በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂና ቋሚ፤ የጽሕፈት፤ የጽዳት፤ የኤሌክትሮኒክስ፤ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ ጎማዎች እና ሞተር ሳይክሎች፤ የመሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕ/ወለጋ ዞን የቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ አላቂና ቋሚ፤
- የጽሕፈት፤
- የጽዳት፤
- የኤሌክትሮኒክስ፤
- የቢሮ ፈርኒቸሮች፣
- የተለያዩ ጎማዎች እና ሞተር ሳይክሎች፤
- የመሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ፤ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ( ሶስት መቶ) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርባችሁ የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ ሲሆን፣
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
1. በዓመቱ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) “ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ (CPO) 2% ከሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ዋጋ ዕቃ ጋር ማስያዝ አለባቸው።
3. የጨረታ ተሳታፈዎች የሚያቀርቡትን ጨረታ የቴክኒክ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን የፋይናንስ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ከ2፡30 – 11፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. የግብር መክፈያ (TIN) ቁጥር ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
5. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ23/1/2017 ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት በኋላ በ13/2/2017 ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን 14/2/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል፡፡
6. በገንዘብ ጽ/ቤት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቅት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
7. ይህን ጨረታ የሚጫረቱ ድርጅቶች የራሳቸውን እስቶር (መጋዘን ) ሊኖራቸው ይገባል።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስምና (Brand name ) የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ናሙና አቅርቦ ማሣት አለበት።
9. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ዝርዝር መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፍነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡
10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ካቀረቡ ይዞ ይመለሳሉ።
11. ማንኛውንም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችሉም።
12. መቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላሉ።
13. ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ለምን ለምን ዓይነት ዕቃ እንዲሆነ በሰነዳቸው ላይ በትክከል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
14. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች ውል ይፈራረማሉ:: ውሉ እንደእስፈላጊነቱ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የሚቆይ ይሆናል።
15. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውንና ማህተም ለይተው በትክከል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
16. በጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት።
17, ተጫራቾች የቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ ከጨረታው መክፈቻ ዕለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ሥራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ጊዜ መግለጽ አለባቸው
18 . አንድ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርስሶ ዋጋ ማቅረብ (መፈጸም አይችልም ።
19. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታው አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ 10% በማስያዝ በቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጥተው ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
20. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸው ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት በቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
21. የእቃዎችን ዋጋ የምንከፍለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኋላ ይሆናል። ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሥር በምንረከበው ዕቃ መጠን ወይም ብዛት ልክ ከፍያ መፈጸም ይቻላል።
22. በወቅቱ ያልቀረበ የጨረታ ሰነድ፤ ከጨረታ ሳጥን ውጭ የተገኘ የጨረታ ሰነድ የባለቤትነት ወይም የሕጋዊ ተወካይ ማስረጃ የሌለው ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
23, በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያልተቀመጠ መስፈርትን ለግምገማ እያለግልም። ጨረታው ሲከፈት ሁከት ማንሳት የተከለከለ ነው።
24. ሁሉም ተጫራቾች በየንግድ ዘርፉ የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
25. ለጨረታው ማስከበሪያ የተያዘ (Cpo) ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊ ድርጅት ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡
26. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 09 21 820 909- 09 17 181 225 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕ/ወለጋ ዞን የቤጊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
