የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሸከርካሪ ጎማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- EEP/ST/NCB/08/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሸከርካሪ ጎማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-1 ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/08/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1. |
የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ |
ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) |
ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 011-5-58-06-27 መደወል ይችላሉ፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል
