Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Oct 2024, 3:38 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጠል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጠል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  • ጋቢናዎቹን ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒከ ማዕከል በመገኘት ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (ETHIOPIAN INSURANCE CORPORATION) ስም ሲ.ፒ.አ. በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

-   የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው::

  • ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፤ ለአሸናፊዎች ግን ሂሣቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልከ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከከፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና ባለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 011439-25-89 እና 011439-25-45 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Save Tender