የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ከጋሰራ አስከ ጊኒር ድረስ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን መከራየት ይፈለጋል
Ethiopian Railway Corporation (የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን)
የማሽነሪ እና ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ከጋሰራ አስከ ጊኒር ድረስ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን መከራየት ይፈለጋል፡፡
ስለሆነም ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድፈቃድያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና እና ሚኒባስ በኪራይ ለማቅረብ ግን የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላለ
4. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ማህበራዊ ገጽ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት (Supplier list) ላይ የተመዘገቡበት
5. የዘመኑን ግብር መገበራቸውን የሚያሳይ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ መረጃ
6. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸዉና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተዉ መቅረብ አለባቸው፡፡
7. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
8. ተጫራጮች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 100,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 (ዘጠና) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር- 32 ይህ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን መስከረም 16/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ጨረታው እስከሚዘጋበት ጥቅምት 6/2017 ዓ/ም ድረስ በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ስዓት መግዛት ይችላሉ።
10. የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎቹን/ቲክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጀርባ ባለው የጨረታ ክፍል ጨረታው በአየር ላይ በዋለ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
12. እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 011-470 2044 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0963-576235 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከጉምሩክ ኮሚሽን ፊት ለፊት ባቡር መሻገሪያው
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ
