የሆለታ ንብ ምርምር ማዕከል በስሩ ላሉት ተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ እቃዎችን ራሱ ገዝቶ በማቅረብ ጋራዦች የሚጠግኑበትን የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት (ለ2017 ዓ.ም) ተሽከርካሪዎቹን ማስጠገን ይፈልጋል
የሆለታ ንብ ምርምር ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆለታ ንብ ምርምር ማዕከል በስሩ ላሉት ተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ እቃዎችን ራሱ ገዝቶ በማቅረብ ጋራዦች የሚጠግኑበትን የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት (ለ2017 ዓ.ም) ተሽከርካሪዎቹን ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣
2. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ቫት የተመዘገቡና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የመድን ዋስትና ኢንሹራንስ ያላቸው
4. ለተሽከርካሪዎቹ ጥበቃና ደህንነት በቂ የማቆሚያ ግቢ ያላቸው
5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00(አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋረጠ ሲፒኦ (cpo) በሆለታ ንብ ምርምር ማዕከል ስም
ማስያዝ አለባቸው፡፡
6. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ) ብቻ በመከፈል ከመስሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አንድ ዋናና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን በዚሁ ቀን ጠዋት 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡እለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
10. የተቀየሩ አሮጌ የመለዋወጫ እቃዎች ለመ/ቤቱ ተመላሽ ይደረጋሉ፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ወልመራ ወረዳ ሆለታ ከተማ ከአዲስ አበባ በአምቦ መስመር በ30 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 011-237-0350 /011-237-0023
የሆለታ ንብ ምርምር ማዕከል
