በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው የሚያስፈልጉትን የተለያዩ እቃዎችና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001ግ/ጨ2017 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው የሚያስፈልጉትን የተለያዩ እቃዎችና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ
- በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ በዌብሳይት የሚረጋገጥ፣
- የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ሁሉ ከቫት ጋር የተሰላ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ነገር ግን የተጨማሪ እሴት ታክስን ያላካተተ ከሆነ ለአሰራራችን አመች ስለማይሆን ለውድድር አናቀርበውም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በጤና ጣቢያው ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መወሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዋናውንና ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማህተምና ፊርማ አድርገው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ (ሲፒኦ)፡-
- ሎት 1 መድሀኒትና ሪኤጀንት 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት 2 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 3 ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃ 8,000 (ስምንት ሺህ ብር)
- ሎት 4 የደንብ ልብስ 6,000 (ስድስት ሺህ ብር)
- ሎት 5 አላቂ የፅዳት ዕቃ 4,000 (አራት ሺህ ብር)
- ሎት 6 ቋሚ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች 7,000 (ሰባት ሺህ ብር)
- ሎት 7 ህትመቶች 5,00 (አምስት ሺህ ብር)
ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ተጫራቾች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በዘርፉ ከተደራጁበት ወረዳ ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት አምራች መሆናባን የሚገልፅ ህጋዊ ደብዳቤ (ሰርተፍኬት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሰነድ መቀበያ ጊዜ ያበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ተዘግቶ በዛው ዕለትና ሰዓት 4፡30 ላይ የመክፈቻ ቃሉ -ጉባኤ ተይዞ ሲታሽን የነበሩ ታዛቢዎችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከአቅራቢዎችም ሆነ ህጋዊ ወኪል ባይገኙ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመክፈቻ ቀንና ሰዓቱ የማይራዘም መሆኑን እንገልፃለን።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሣለሚያ ወደ 18 አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ ከበለስ ሆቴል ትንሽ ገባ ብሎ ወይም ባለሶር ህንፃ በስተጀርባ በኩል የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ -
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 0112 73 70 72 መደወል ይችላሉ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
