የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፍትህ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጽህፈት መሳሪያዎች እና የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Central Ethiopia Justice Office
የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፍትህ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጽህፈት መሳሪያዎች እና የኤሌከትሮኒክስ
እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሎች ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ/መስሪያ ቤቱ ግዥ፣ ከፋይንንስን ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር ቁጥር 19 በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት በ50 ብር በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታከስ ጨምሮ ያቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት /በ16ኛው ቀን /ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
16. የጽህፈት መሳሪያዎች ተጫራቾች የተወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና (Sample) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
17. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች መስሪያ ቤታችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት::
18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
ነው::
19. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀን ድረስ የፀና ይሆናል፤
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0465562550/0916239206 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በማ/ዕ/ኢ/ክ/መንግስት ግዢ፣ ፋይናንስና
ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
