Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Aug 2024, 2:20 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Banking Equipment And Services

አዋሽ ባንክ አ.ማ. አክሲዮኖች ለመሸጥ ይፈልጋል


የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

አዋሽ ባንክ አ.ማ. የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 ከመውጣቱ በፊት የውጭ ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን የሚከተሉትን አክሲዮኖች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ምድብ ሎት 

ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ የቀረቡአክሲዮኖችሰርተፍኬት ቁጥር

የአክሲዮኖቹ ብዛት

 

የአንዱ አክሲዮን መነሻ ዋጋ

 

የአክሲዮኖቹ ጠቅላላ መነሻ ዋጋ

 

1

20223 እና0037992

180

1,000.00

 

180,000.00

 

2

24416 እና 24468

19

1,000.00

19,000.00

3

42865 እና0035254

2

1,000.00

 

2,000.00

 

በመሆኑም፡-

  1. የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/73/20 ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የውጭ ዜጎች እና ድርጅቶች በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው በመሳተፍ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ቀን በፊት ከባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ብር 200 (ሁለት መቶ) ከፍለው በመውሰድ ቅጹን ሞልተው በኤንቨሎኘ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ድረስ ከባንኩ ዋና መ/ቤት ጀርባ ባንኩ በተከራየው ኢያሜክስ ህንፃ የመሬት ወለል ላይ ባለው የባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነዱን ባስገቡበት ቦታ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ የሚሆን አክሲዮኖቹን ተጫርተው የሚገዙበትን ዋጋ 1/4 (እሩቡን) በአዋሽ ባንክ ስም በተሠራ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች በቀረበ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  6. በአንድ ሎት (ምድብ) የቀረቡ አክሲዮኖችን ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ መጫረት አይቻልም፡፡
  7. ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ደግሞ ቢጫ (የሎው) ካርድ እና ፓስፖርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሲሆን ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ካሸነፉም ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ብቻ ነው፡፡ 
  9. የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት /5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ተሰርዞ ለጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  11. ተለያይተው የቀረቡትን ሎቶች (ምድቦች) መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ምድብ (ሎት) በተለያየ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ ማስያዣ ሲፒኦውም ተለያይቶ መቅረብ አለበት፡፡
  12. በሌሎች ሕጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
  13. ባንኩ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

“ይህ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ እንዲተላለፍ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ማረጋገጫ አግኝቷል” አዋሽ ባንክ
ስተጨማሪ መረጃ 0115-57-00-92/0115571823
ፖ.ሣ.ቁ 12638
አዲስ አበባ


 

Save Tender