ሕብረት ባንክ አ.ማ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አማ በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
|
ተራቁ |
የቅርንጫፍ ስም |
የተበዳሪ ስም
|
የአስያዥ ስም
|
ቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ባምቢስ |
አቶ ዓብይኃይለ ማርያም ማሞ |
አቶ ዓብይኃይለ ማርያም ማሞ |
አዲስ አበባ፣የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11፣ የቦታ ስፋት 230 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ G +3 የሆነ ቤት! |
AA000051104797
|
37,732,999.00
|
ነሃሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 |
|
2 |
አራዳ ሻሸመኔ |
እነወይ/ አናጂአማን አደም |
ወይ/ አናጂአማን አደም |
ሻሸመኔ ከተማ፣አራዳ ክ/ከተማ የሚገኝ፣ የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ የሆነ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት፤ |
3602 |
2,672,635.00
|
ነሃሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው በሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ ደግሞ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና አስያዦች ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ጽሑፍ፣መተዳደሪያ ደንብ፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተው ጨረታ ቀደም ሲል ሰኔ 09 ቀን 2016 ዓ.ም. በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ጨረታውን ለማካሄድ ለሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ተሰርዞ እንደገና ሊወጣ ችሏል፡፡
- ገዥ(የጨረታው አሸናፊ) የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ(ግብር) እና የስም ማዛወሪያ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡ ባምቢስ ቅርንጫፍ ፡ 0115 57 89 30፣ አራዳ ሻሽመኔ ቅርንጫፍ፡ 0462 11 44 43/45 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ ፡ 0114 70 03 15/47 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
