Hibret Bank ስመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸዉ ብድሮች በመያዣነት የያዛቸዉንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል::
|
ተራ ቁጥር |
የቅርንጫፍ ስም |
የተበዳሪ ስም |
የአልያዥ ስም |
በቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታ ስፋት |
የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
የሐራጂ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ሂልተን |
አርሆታይ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
አርክቴክት ዮሴፍ በረደድ እና ዶ/ር መመናሻ ኃ/ጊዮርጊስ |
ኦሮሚያ ክልል፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ቀበሌ 01፣ የፓርሴል መለያ ቁጥር CCD/33B፣ የቦታ ስፋት 1,026.5 ካ ሜ የሆነ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ባለአንድ ፎቅ ቤት፤ |
L/X/L/D/9962/012 |
20,478,998.00 |
መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
|
2 |
አረብ ሰፈር ሀዋሳ |
አቶ ግዛው ለገሰ ላላሞ |
ወ/ሮ መብራት ቱርቦ ቱሞ |
ሀዋሳ ከተማ፣ ታቦር ክ/ከተማ ሂጠታ ቀበሌ የሚገኘውን ፣ የቦታ ስፋት 200 ካ ሜ የሆነ ለመኖርያ አገልግሎት የሚውል ቤት |
15875 |
3,758,872.00 |
መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
2. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል::በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል::
3. የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው::
4. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ተበዳሪዎች እና አስያዦች ናቸው::ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል::ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመሥረቻ ጽሑፍ፣መተዳደሪያ ደንብ፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት::
5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል::
6. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል::
7. ገዥ(የጨረታው አሸናፊ) የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ(ግብር) እና የስም ማዛወሪያ ይከፍላል::
8. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- ሂልተን ቅርንጫፍ- 0115 15 15 34/0115 53 68 46 ሀዋሳ ቅርንጫፍ: 0462 20 42 68/ 43 39 ወይም ሕግ አገልገሎት መምሪያ፣ 0115 57 37 72/0114 70 4103 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
