የሁለተኛ ዙር የደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
ከዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በቁጥር 3063/ፋ 6 በ23/12/2015 ዓ/ም በተፃፈው ደብዳቤ መሰረት ዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር 06/በ2016 ዓ/ም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን በማረቃ ወረዳ በጎዞ ባሙሺ ቀበሌ እና በጎቦ ሻመና ቀበሌ ውስጥ ያለውን የሰው ሰራሽ የሆነውን ያባህር ዛፍ ደን ያረጀና ዕድሜውን የጨረሰ በመሆኑም ይማረቃ ወረዳ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች በዝርዝር የተግለጸውን መመዘኛዎችን የሚያJሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው
- የዘመኑ ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ቫትን ጨምሮ /tin/ ተመዝጋቢ የሆነ
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000/አምስት ሺህ/ ብር በባንክ የተዘጋጀ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ብቻ የታሸገ ፓስታ በማቅረብ በመ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን መጨመር ይኖርበታል።
- በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም
ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከመ/ቤቱ ግዥ ንብረት አስ/ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ቀርባችሁ ማረቃ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በማረቃ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ት በኩል ጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ዋጋ ማቅረቢያ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀን ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ
- ጨረታው ተጫራች ቢገኙም ባይገኙም ሊከፈት ይችላል።
- የራሳቸው ዋጋ ማቅረብ ያላቸው ተጫራቾች በራሳቸው ዋጋ ማቅረቢያ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
- የመክፈቻ እለት ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- ጨረታውን ያለፈ ድርጅት ጨረታውን አልፎ ውል ከገባበት በሶስት ወር ውስጥ ደኑን ቆርጦ ማንሳት መቻል አለበት
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር ፦ 0948999120,0917505987,0917402738
የዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
