Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Jan 2024, 1:02 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Government Treasury Bill

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


በፍባለመብት እነ አቶ መስፍን ሀይሉ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ህፃን ሣምሶን ሃይሉ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጸጻም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 301912 በ29/2/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት አ/አ/ከተማ የካ ጣፎ ሳይት በአዲሱ አደራጃጀት ለሚ ኩራ ክ/ከተማ በJች አቶ ሀይሉ ለታ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ቤት የቦታ ስፍት 92 ካ.ሜ የሆነው  የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,831,012 /አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሠላሳ አንድ ሺ ብር ከ12 ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። ተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ የጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጽም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመጦቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡00 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀረበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.p.o ማስያዝ ይኖርበታል።

ከ1/4ኛ አስበልጦ ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።

በጨረታው አሽናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጲያ ንግድ ባንከ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡነ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

 

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/በቶች የፍርድ

አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

Save Tender