የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2016
በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገልጽትን ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የህትመቱ ዓይነት | መለያ | ብዛት |
| 1 | የቀበሌ ደረሰኝ(መዐጤመ) | ማ/ሂ/1 | |
| 2 | የዕቃ ወይም ንብረት ገቢ ደረሰኝ(መዐጤመ) | ማ/ሂ/ጤ/ሞ 22 | 10, 000 |
| 3 | የዕቃ ወይም ንብረት ወጪ ደረሰኝ (መዐጤመ) | 500 | |
| 4 | የወረዳ ገቢ ደረሰኝ (መዐጤመ) | ማ/ሂ/ጤ/ሞ 22 | 500 |
| 5 | የክፍያ ሰነድ (መዐጤመ) | ማ/ሂ/7/ለ | 500 |
| 6 |
የተጠቃለለ የገቢ ደረሰኝ (መዐጤመ) |
ማ/ሂ/ጤ/7/1 | 500 |
| 7 | የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ(መዐጤመ) | ማ/ሂ/64 | 500 |
| 8 | የሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ (መዐጤመ) | ማ/ሂ | 200 |
| 9 | ሌጀር ካርድ (መዐጤመ) | ማ/ሂ/11 | 5000 |
- በአቅራቢያዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚችል
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት/Tin Number/ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣
- ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጅውን ሰነድ ሀዋሳ በሚገኘወ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 1 የማይመለስ 100 00/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይቸላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይውላል።
- ተጫራቾች ጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 01 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት ይከፈታል። ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጽው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ማስያዝ አለባቸው።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 046-212-01-16 መደወል ይችላሉ።
