መ/ቤታችን የላብ ቶፕ ኮምፒውተር /Procurement of Laptop Computer/ ግዥ በካልም በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| የሚገዛው የአገልግሎት አይነት |
| የላፕቶፕ ኮፒውተር ግዥ /Procurement of Laptop Computer/1. |
1. የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ስታቲስክስ አገልግሎት ዋና መ/ቤት በመምጣት የማይምለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN NO/የተ.እ.ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት እዲሁም የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጽም ቃል የሚገባበትን ቅጽ በመሙላት ፊርማ ማህተም በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ለጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር የኢትዮጵያ እስታቲክስ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ትክክለኛ አድራሻ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በማየት የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓ አስቀድሞ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ተያይዞ ያልቀረበ ወይም ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት አስቀድሞ ያልቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የቢሮ አገልግሎት በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
5. የሚወዳደሩበት ሰነድ አንድ ኦርጅናልና እንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታቶ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የኢትዮጵያ ስታቲክስ አገልግሎት ዋና መ/ቤት በዚሁ ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ መዝጊያ መክፈቻ ይሆናል።
6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሚሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
