Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Jul 2023, 2:19 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Materials

የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ፓርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት አሸዋ ጠጠር እና ድንጋይ ግዥ በመስኩ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ በጨረታ አወዳድሮም መግዛት ይፈልጋል።


1..ተጫራቾች የዘምነኡ ግብር የከፈሉ መሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ የሚቀርቡና በስሙ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝርዝ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. የጨረታ ሰነዱ ከ ሰኔ 9ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የኢ.ኤ.አ ፕሮጀክቶች ፓርትፖልዮ ማኔጅመት ጽ/ቤት ከከቴደራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ እሪ በከንቱ በሚባለው አካባቢ በርጌስ ክሊኒክ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትን /Irrivocuble Uncondtional Bank Guarantee/ጨረታ ፀንቶ ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው በኢ.ኤ.አ ፕሮጀክት ፓርትፖልዮ ከማኔጅመንት ወይም EEU-UEAP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱጋር ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU/PMM/28/2015/NCB/ የሚል ምልክት በማድረግ አስከ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ  የኢ.ኤ.አ ፕሮጀክቶች ፓርትፖልዮ ማኔጅመት ጽ/ቤት ከከቴደራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ እሪ በከንቱ በሚባለው አካባቢ በርጌስ ክሊኒክ ህንፃ ላይ 3ኛ ፎቅ በመቅረብ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም/ሰኔ 23ቀን 2015 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል።

6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱ ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰአት ከሰዓት ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአካል መጥቶ በመግዛት ሙሉ መረጃውን መመልከት ይችላሉ።

7. የኢ/ኤ/አ/ፕ/ፖ/ማ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111275503/3159 መደወል ይችላሉ።

Save Tender