በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከል የወንዝ አሸዋ (River Sand) ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡-ኢኮስኮ ግ/ማ/ማ 15/2015
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከል የወንዝ አሸዋ (River Sand) ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ታክስ ክሊራንስ እና በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ፤
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6:30 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከል በባንክ በተዘጋጀ ሲፒኦ ወይም Unconditional Bank Guarantee የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለብቻው በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በማስላት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻው ቀን ሚያዝያ 30/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 30/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 የግብዓት ማምረቻ ማዕከል ቅጥር ግቢ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው የጨረታ ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው።
- ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ፡- ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፤
አድራሻ- ደብረዘይት መንገድ ቃሊቲ ማሰልጠኛን አልፎ ወረዳ 05 አጠገብ ግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት
የፖ.ሣ.ቁ፡-102365
ስልክ ቁጥር፡- 0913-16-56-30
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከል
