የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የመንገድ ደህንነት ዕቃዎች አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ግጨቁ. 43/2015
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አቅርቦት ፍላጎት ካላቸው የሃገር ውስጥ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
- የመንገድ ደህንነት ዕቃዎች አቅርቦት
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- ቫት ተመዝጋቢ
- ታክስ ክሊራንስ
- የግዥ ኤጀንሲ የምዝገባ ማስረጃ
- የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት
- በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ወረቀት
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 90 ( ዘጠና ) ቀናት
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 100,000.00 (መቶ ሺህ) ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መሆን ይኖርበታል ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ. ቁጥር 01 የማይመለስ 300.00(ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ::
- የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት 03/ 09/2015 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት
- ጨረታው የሚከፈተው፡- በዕለቱ 03/09/2015 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 011 417 17 03 መጠየቅ ይቻላል::
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ (ዋና መስሪያ ቤት ቱሉ ዲምቱ)
