በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዳኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የመፀዳጃ ቤት ግንባታ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዳኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት በኩል በኮዋሽ ፕሮጀከት ድጋፍ የሚሰራ የስድሳ ዳዳኮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፦
- ለ2015 በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- TIN ቁጥር ያለውና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ግብር የከፈለበትን መረጃ የሚያሳይ ክሊራንስ ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችል
- በወቅቱ ገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የመጫረቻ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20,000 /ሃያ ሺህ/ በደኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ የሚችል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በደኤላ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ሰነዱን ከዳኤል ወረዳ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይና በ22ኛው ቀን የመጫረቻ ሰነዱን ዋናውንና ሁለት ኮፒ ቴክንካልና ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግ ህጋዊ ማህተም በመምታት በትልቁ ፖስታ በማድረግ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ 2፡30 – 5፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፣ የጨረታ ሳጥኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ እና የበዓል ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተባለው ቦታ 7፡30 ሰዓት ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0994174961 / 0925156662 / 0910498942
በሲዳማ ክልል የዳኤል ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
