Tender Detail

Tender Details

  • Deadline17 Apr 2023, 4:40 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Promotional Items

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ የፅዳት ዕቃዎች ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የህትመት ውጤቶች ፣ ጫማ እንዲሁም ኤፕረን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 03/2015

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ

  1. የፅዳት ዕቃዎች፣
  2. የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  3. የህትመት ውጤቶች፣
  4. ጫማ፣
  5. ኤፕረን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፡_

  1. የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በሚገኘው ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 150.00 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ውሰድ ይችላሉ።
  3.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለየምድቡ (ሎት) የተመደበውን የብር መጠን በCPO ማስያዝ አለባቸው። ከአንድ በላይ በሆነ ሎት የሚሳተፉ ተጫራቾች ለየሎቱ የተመደበውን የብር መጠን ድምር በCPO ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነዶች እና የሞሉትን ዋጋ ዋና እና ኮፒ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጣዋቱ 4፡00 ድረስ (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ተጫቾች ዋጋ ማቅረብ ያለባቸው ከጤና ጣቢያው በሚወስዱት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብቻ ነው።
  7. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። የህትመት ውጤቶች ጤና ጣቢያ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት የሚዘጋጁ ይሆናል።
  8. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስሙ ሰሜን ማዘጋጃ ስልክ ቁጥር 011 812 6804/12 29 60 ሰሜን ጤና ጣቢያ

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ

 

 

Save Tender