Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Apr 2023, 4:28 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Engineering Service

በአ.ብ.ክ.መ ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2015 በጀት ዓመት የመሬት ሀብት ቆጠራ እና ፋይል ማደራጀት ሥራ ለማሠራት እንዲቻል አማካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል


በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአ.ብ.ክ.መ ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2015 በጀት ዓመት የመሬት ሀብት ቆጠራ እና ፋይል ማደራጀት ሥራ ለማሠራት እንዲቻል አማካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት፡

  1. በዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ክፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 19,500.00 በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ( CPO ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በመሬትና መሠረተ ልማት ሀብት ቆጠራ ላይ የሠሩና መረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
  7. የመሬት ሀብት ቆጠራ እና ፋይል ማደራጀት ሥራን በተመለከተ አሸናፊው ተጫራች ከአሸነፈበት በጀት ላይ ተቀንሶ ለተቋሙ 10 መሀንዲሶች ስለመሬት ቆጠራና ፋይል አደረጃጀት ዙሪያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ዕውቅና የሚሠጥና ሥራውንም የሚያለማምድ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፣ ፋይ/ንብ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል። (ባይገኙም ይከፈታል ) የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይፈፀማል።
  10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን ፣ በጨረታ ሠነዱ የሠጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
  11. የሂሳብ ስሌት ( አርቲሜቲክ ቼክ ) በግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሠነድ ላይ በነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  12. የሚሠሩት የመሬት ሀብት ቆጠራ እና ፋይል ማደራጀት ሥራዎች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት።
  13. አሸናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነው።
  14. ጽ/ቤቱን በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች ብዛት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
  15. አሸናፊው ድርጅት ሥራዎችን ጥራቱን ጠብቆ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-222-0162 ደውሎ መጠየቅ ይችላል ።

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን

Save Tender